Ethiopian Lutheran Church,  Mekane Yesus in Minneapolis (ELCA)

አራቱ መንፈሳዊ ሕጎች

ለማንኛውም ነገር ደንብና ሥርአት እንዳለው ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ የዘላለምን ሕይወት ለማግኝት ደንብና ሥርዓት አለው። መጽሓፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተስጠን የደንብና የስርዓት መጽሐፍ ነው።

1 ኛው ሕግ
እግዚአብሔር ስለሚያፍቅር ዎት ለሕይወትዎ አስደናቂ የሆነ እቅድ ስጥቶዎታል። 

 

 

የእግዚአብሔር ፍቅር
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።ዮሐንስ 316
    ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።   ዮሐንስ 1427

    2 ኛው ሕግ
ሰው  ሐጥያተኛ  ባህርይ ስለ አለውና በዚህም ምክንያት  ከእግዚአብሔር ስለተለየ እግዚአብሔር ለርሱ ያለውን ፍቅርና  እቅድ ሊለማመድ  አይችልም

ሰው ኃጥያተኛ ነው
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል”   ሮሜ 3 23
ሰው የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጅ  እንዲሆን ትፍጥሮ ነበር ነገር ግን ሰው የገዛ መንገዱን ስለተከተለ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ወዳጅነት ተቋረጠ።  ይህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ኃጥያት እያለ የሚጠራው። ሰው በእግዚአብሔር ላይ እንዳመጸ ።ለእግዚአብሔር ፍቅር ግድ እንዳልነበረው።ፍጹም በሆነው በእግዚአብሔር ላይ መደገፍንና   መተማመንን እንዳልፈለገ ነው።
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ “      ሮሜ 623
3ኛው ሕግ  ለዚህ ችግር መልስ ይሰጠናል

      3ኛው  ሕግ
እየሱስ  ክርስቶስ  ለእኛ በመሞቱ በእርሱ በኩል ብቻ ሰው ወደ እግዚአበሔር ይደርሳል።  በእርሱም በኩ እግዚአብሔርን ለማወቅና የዘላለም ሕይወትን ለናግኘት  ንደዚሁም ለሕይወትዎ ያለውን እቅድ ለማወቅ ይችላሉ፤ ይህም የሆነበት በቂ ምክንያት አለ።
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ”  ጴጥሮስ 118

ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው
             ሐዋርያት ሥራ 13
          መንገዱ ኢየሱስ ብቻ ነው !
እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ”  ዮሐንስ 146

እግዚአብሔር አምላክ በሰውና በርሱ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥፋት እንድንችል ልጁን እየሱስ ክርስቶስን በኛ ፈንታ በመስቀል ላይ እንዲሞት ልኮታል እንዚህን ሶስቱን ሕጎች ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም።

4ኛው ሕግ
እየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኛችንና ጌታችን አድርገን በመቀበል እግዚአብሔር አምላክ  ለእኛ ያለውን ፍውርና እቅድ ልናውቅና ልንለማመድ እንችላለች።
 ክርስቶስ በእምነት ልንቀበለው ይግባናል
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው   ዮሐንስ 112“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤  ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለምኤፌሶን 28-9 ወደ ሕይወታችን እንዲመጣ በሙሉ ልባችን በመጋበዝ ክርስቶስን ለመከተል ዛሬ እንወስንእነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላልራዕይ320 ከእየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ጋር ብቻ መስማማቱ በቂ አይደለም  ክርስቶስን መከተል ማለት ከገዛ ራስ መንገድ ወደ እግዚአብሔር መንገድ መመለስ ማለት ነው
እየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወታችን በመምጣት ኃጥያታችንን ይቅር እንድሚለን እናምናለን።የሚከተለው ሃሳብ ክርስቶስን እንዴት ለመከተል ስለመወስን ያሳያል።ወደ ሕይወትዎ እንዲመጣ ጋብዘው የሰጠውን ተስፋ ማድረግ እንደሚችል ይመኑት፤ እርሱም በቃላት ከሚገልጽዋቸው ኃሳቦች ይልቅ በይበልጥ በልብዎ ስለሆነው ፈቃድ ይገደዋል ።ከላይ ከተዘረዘሩት መንፈሳዊ ሕግጋት ጋር ከተስማሙና ክርስቶስን ለመከተል ከወሰኑ ይህን ጸሎት ይጸልዩ ።ጌታ እየሱስ ሆይ ዛሬ ኃጥያተኛ መሆኔንና ለእኔ  ኃጥያት ስትል  ህይወትህን በመስቀል ላይ እንደሰጠህ  አምኜአለሁ፤  በደሌን ሁሉ ይቅር በለኝ ቀይረን የዘላለምንም ህይወት ስጠኝ፤ ጸሎቴን ስለሰማህ አመሰግናሀለሁ፤ አሜን